አንድ አሜሪካዊ የሥራ ባልደረባዬ ተሁለት ሳምንታት በፊት አለወትሮው ቆጣ ብሎ ጸጉሩን እየነጨ ሲትከነከን አገኘሁት። “ምነው በመላጣህ ምክንያት የቁንጅና ውድድር ወደክ ወይስ የቀጠርካት ጉብል ቀረቺብህ!” ብዬ ልቀልድ ብሞክርም አለወትሮው ከንፈሮቹ አልሳሳ ጥርሶችም አልታይ አሉ። ሁለቴ ጠበቅ አድርጎ “እፍፉ…” ብሎ ታምቆ የቆዬ እስተንፋስ ከተነፈሰ በኋላ “ይህ ትራንፕ እሚባል ሰው ተቀናቃኙን ለማጥቃት ስልጣኑን መጠቀሙ ቅደመ አያቶቻችን የመሰረቱትን የአሜሪካ […]
↧