ከአንድ አመት በፊት የሳውዲ አረቢያ መንግስት በህገወጥ መንገድ የሚኖሩ የውጭ ሃገር ዜጎች ግዛቱን ለቀው እንዲወጡ ያስቀመጠው የግዜ ገደብ መጠናቀቁን ተከትሎ አያሌ ኢትዮጵያውያን ጅዳ እና ሪያድ ከተማ ወደሚገኙ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ መጉረፋቸው ይታወሳል። በወቅቱ ከነበረው ስርዓት አልበኝነት ህይወታቸውን ለመታደግ አቅሙ የቻለ ጎረምሳ ልብሶቹን በሻንጣ አጭቆ እግር አውጭኝ ሲል አይን ያልገለጹ ህጻናት ልጆቻቸውን በወጉ መሰብሰብ ያልቻሉ እናቶች [...]
↧