ዶክተር ሬዶልፍ ክኑት ሞልቨር (Reidulf Knut Molvær) የ77 ዓመት ኖርዌጂያዊ አዛውንት ናቸው። ዋና ሙያቸው የሥነ ጥሑፍ፣ የቋንቋ፣ የታሪክና የማህበራዊ ሳይንስ ተመራማሪነት ነው። በአማርኛ ሥነ ጽሁፍና ቋንቋ ጥናት ከሎንዶን ዩኒቨርስቲ የዶክትሬት ድግሪያቸውን ያገኙ ሲሆኑ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ 14 ኬንያ ውስጥ ደግሞ 6 ዓመታትን ባለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ በመሥራት አሳልፈዋል። የትዳር ጓደኛቸው ኬንያዊት ሲሆኑ፣ አራት ልጆችም በጋራ አፍርተዋል። [...]
↧